بِسۡمِ ٱللهِ ٱلرَّحۡمَـٰنِ ٱلرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ٱقۡرَأۡ بِٱسۡمِ رَبِّكَ ٱلَّذِى خَلَقَ (١) خَلَقَ ٱلۡإِنسَـٰنَ مِنۡ عَلَقٍ (٢) ٱقۡرَأۡ وَرَبُّكَ ٱلۡأَكۡرَمُ (٣) ٱلَّذِى عَلَّمَ بِٱلۡقَلَمِ (٤) عَلَّمَ ٱلۡإِنسَـٰنَ مَا لَمۡ يَعۡلَمۡ (٥)
"አንብብ፣ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም። ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡ አንብብ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤ ያ በብርዕ ያስተማረ፤ ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳዎቀ ሲኾን፡፡"
ቅዱስ ቁርዓን ምዕራፍ 96 ከቁጥር 1-5

Amharic Translation Of Holly Quran የቅዱስ ቁርዓን አማርኛ ትርጉም

*******بِسۡمِ ٱللهِ ٱلرَّحۡمَـٰنِ ٱلرَّحِيمِ*******

وَٱلۡعَصۡرِ (١) إِنَّ ٱلۡإِنسَـٰنَ لَفِى خُسۡرٍ (٢) إِلَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّـٰلِحَـٰتِ وَتَوَاصَوۡاْ بِٱلۡحَقِّ وَتَوَاصَوۡاْ بِٱلصَّبۡرِ (٣) "በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡" "በጊዜያቱ እምላለሁ፤ ሰው ሁሉ በእርግጥ በከሳራ ወስጥ ነው፡፡ እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሰሩት፣ በእውነትም አደራ የተባባሉት፣ በመታገስም አደራ ተባባሉት ብቻ ሲቀሩ፡፡" ***ቅዱስ ቁርዓን ምዕራፍ 103*** አሰላሙ አለይኩመ ወረህመቱላሂ ወበረካቱ፡፡ ሰላም እና ደህንነት በእናንተ ላይ ይሁን፡፡ በመጀመሪያ እንኳን ደህና መጡ፡፡ ይህ የኢንተርኔት መረብ ለአለም የሰው ልጅ ዘር በሙሉ ተብሎ የተዘጋጀ ነው፡፡ በነገራችን ላይ የሰው ልጆች ሁሉ ሲፈጠሩ ሙስሊሞች ናቸው፡፡ ሆኖም ወላጆቻቸው በልጅነታቸው ክርስቲያን፣ አይሁድ ወይም የሌላ እምነት ተከታይ እንዲሆኑ ያደርጓቸዋል፡፡ በትክክል የሚያገናዝብ ሰው ግን ፈፅሞ በወላጆቹ ተፅኖ ሳይበገር እድሜው እውነትን ከስህተት መለየት ሲጀምር አላህ እውነትን እንዲመረምር ይወድለታል፡፡ ለዚህም ነው ዛሬ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች፣ አይሁዶች ወይም ፈፅሞ እምነት የለላቸው ሰዎች ወደ ኢስላም አየጐረፉ የሚገኙት፡፡ አላህም በቅዱስ ቁርዓኑ እንደሚያስተምረን በዚህ አለም ላይ ከእስልምና ውጭ ሌሎች እምነቶች ሁሉ ውድቅ (ፈፅሞ የማይጠቅሙ) ናቸው፡፡ ከዚህ ላይ በዋነኛነት ልገልፅ የምፈልገው ነገር ቢኖር፤ ማንኛችንም ብንሆን የቁርዓንን ትርጉም አውቀን ለእምነቱ ያለንን እውነተኛ ገፅታ እናንፀባርቅ፡፡ ከተኛንበት የዚች አለም ህልም ባንነን አላህ በመጨረሻው አለም ላዘጋጀልን ዘልአለማዊ ህይዎት ታጥቀን እንስራ፡፡ ወቢላሂ ተውፊቅ፤ ወሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ፡፡

In the name of Allah most Gracious the most Merciful بِسۡمِ ٱللهِ ٱلرَّحۡمَـٰنِ ٱلرَّحِيمِ

MAY PEACE AND BLESSING BE UPON YOU

I would like to welcome you to the web. This is the website which is created for the whole humankind in this world. Actually humankind is created in Islam by nature, but their families convert them to Christianity, Jewish or any other religion. But there is no any religion rather than Islam. Islam is the only religion given to the whole humankind. My point is that, let us tray to understand what our HOLLY QURAN is telling us. We are sleepy to read and understand the last testament given to prophet Mohammed (P.B.U.H) which is HOLLY QURAN. It is the only book which gives you full answer for any kind of questions in your mind. The main objective of this site is to remind each other about our DEEN (our religion).

Thursday, March 11, 2010

Ya Ekhwani We-akhewat where are we?

O Muslim brothers and sisters where are we? Let us wake up and seek help from the Almighty Allah to help us in our life here and hereafter. Please watch this short very sensitive lecture. Jezakumullahu Kheyren. If you can't see the video please follow this Link the importance of ...

Monday, January 11, 2010

Please listen this BEAUTIFUL QariAselamualeykum Werehmetullahi Weberekatu brother and sisters in Islam.
please listen this beautiful Qari. please forward the link for any one you know.
this is the link NICE QAURAN RECITER

Monday, August 10, 2009

Remedan Kerim Ya Ehwanel Muslimin

Alhamdulillah Asolatu Weselamu Alaresulillah (S.A.W) ya Ehwanel Muslimin
Inshallah we will join our beautiful month of REMEDAN. Alhamdulillah we are here again to join this blessed month. I would like to say REMEDAN KERIM. I would like also to remind my self first and all Muslim brothers and sisters to keep in mind that, don't miss this beneficial month to use it properly. Do any thing which is beneficial both in this world and in the hereafter. Make dua, stikhfar, Sollah, Read Quran,Sodeqa (charity), DEAWA, everything you can. May Allah reward us here and in the hereafter Inshallah. Weahiru Dewana Anilhamdulillahi Rebil Alemin. Weselamu Aleykum Werehmetulahi Weberekatu.

Please click the link below and read this beautiful article.
Messege for remedan.

Wednesday, June 3, 2009

NUIMAN Nice Speech PART-2If you can't watch it, go to the link below and clik on blog archive of June
www.qtinamharic.blogspot.com
JEZALELLAH!

Thursday, May 28, 2009

Thursday, March 5, 2009

ተፈኩር (ማስተንተን)


በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
በመጀመሪያ አላህ ስራቸውን ከወደደላቸው ሰዎች እንዲያደርገንና ነገ የውመልቂያማ ከሱ ጥላስር ከሚያደርጋቸው ሰዎች እንዲያደርገን ለዛ ለታላቁ እጅግ አዛኝ፣ እጅግ ርህሩህ፣ ለሆነው አንድና ብቸኛው ጌታቸችን አላህ ሱብሃነሁ ወተአላ መልእክቴን አደርሳለሁ፡፡ ስራየም ኢህላስ አንዲኖረው ዱአ እንድታደርጉልኝ እየለመንኩ የአላህ ፈቃድ ከሆነ ለዛሬ ያዘጋጀሁትን ላካፍላችሁ በተወዳጁ ነብያችን ረሱል (ሰ.ዓ.ወ)ንግግር እጀምራለሁ ፡፡ "በሊኹ አኒ ወለው አያ" (ከእኔ የሰማችሁትን አንድም ቃል ብትሆን አድርሱ፡፡) ይህ በእያንዳአንዱ ሙስሊም ላይ የተጣለ ሃላፊነት ነው ፡፡

ረቢሽረህሊ ሶድሪ ወየስርሊ አምሪ ወህሉል ኡቅደተ ሚንሊሳኒ የፍቀሁ ቀውሊ። አሚን

ኢንሻላህ ሁላችንም ሙስሊሞች በዚህ አለም ስንኖር ማንኛውንም ነገር ስንሰራ ምክንያታዊ መሆን አለብን፡፡ ለምንሰራው ማንኛውም አይነት ስራ በመጀመሪያ ህሊናችን ለምን እንደሚሰራው ማዎቅ ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም ማንኛዋም የምንሰራት ስራ ተጠያቂነትን ስለምታስከትል ነው ፡፡ ለዚህም አላህ በቅዱስ ቁርዓኑ "የብናኝ ክብደብ መልካም የሰራ ሰው ያገኘዋል፡፡ የብናኝ ክብደት ያክል መጥፎ የሰራም ሰው ያገኘዋል፡፡" ሱረቱ (አል ዘልዘላህ ቁጥር 7 እና 8)የሰው ልጅ ደግሞ የማገናዘብ ችሎታን አላህ ስለሰጠው ይህን ችሎታውን መጠቀም መቻል አለበት፡፡ እንስሳ ብቻ ነው የማገናዘብን ችሎታ ያልተሰጣቸው፡፡ በሁለት ሰዎች መካከል በነበረ አለመግባባት ምክንያት ህሊናየ ብዙ ነበሮችን ያስተነትን ነበር፡፡ ኢንሻአላህ ዛሬ አላህ ከፈቀደ ከዚሁ በመነሳት ነው ይህን አጭር ጽሑፍ (አርቲክል)ለራሴና ለሙዕሚን ወንድሞቸ እና እህቶቸ ለማዘጋጀት ያሰብኩት፡፡
በመጀመሪያ ሙእሚኖች ሁሌም በተፈኩር (በማስተንተን)ላይ ናቸው፡፡ ሲቆሙ፣ ሲቀመጡ፣ ሲተኙ፣ ሲራቡ፣ ሲጠሙ፣ ሲደሰቱ፣ ሲያዝኑ፣ ሲታመሙ፣ ጤነኛ ሆነው ብቻ በማንኛውም ሰአት፣ ሁኔታና ቦታ ላይ ሆነው ተፈኩር ላይ ናቸው፡፡ ሲራቡ የጀሃነብ ረሃብ ያስታውሳሉ፡፡ አላህ ለጀሃነብ ሰዎች ያዘጋጀላቸውን ምግብ (ሸጀረተ ዘቁም የሚባል)ምግብ ይሰጣቸዋል ሲበሉት ርሃባቸውን የበለጠ ይጨምረዋል፤ ፈጽሞ ርሃባቸውን አያስታግስላቸውም፡፡ ሲጠሙ ደግሞ የጀሃነም ጥማት ያስታውሳሉ፤ የጀሃነብ መጠጥ እጅግ የሚያስቀይም ከመሆኑ ባሻገር ትኩሳቱ ገና ሳይጠጡት በፊት የፊታቸውን ቆዳ ገንጥሎ አፅማቸውን ያስቀረዋል፡፡ ግን ይጠጡታል፤ ምክንያቱም ከዚህ የባሰ ጥማት ይዟቸዋል ማለት ነወ፡፡ ጥማቱ ሳይወገድላቸው የሆድ እቃቸውን በመቀመጫቸው ያወጣዋል፡፡ አላህ ይጠብቀንና ይች ጀሃነም አላህ ሲፈጥራት መቀጣጠያዋን የሰው ልጆችና ደንጋዮች አድርጓታል፡፡ ሱብሃነላህ ግን የሰው ልጆች ስንባል ሁሌም ታለቅ እንቅልፍ ላይ ነን፡፡ ሁሌም ዝንጉዎች ሁነን ነው አንጂ አላህ ከዝች ጀሃነብ እንዲያርቀንና አንዲጠብቀን ሌት አና ቀን በለፋን ነበር፡፡ ዳሩ ግን የሰው ልጆች ነንና እርስ በራሳችን መተዋወስ አለብን፡፡ አላህም በቅዱስ ቃሉ "አስታውስ ማስታዎስ ለነዚያ ላመኑት ሰዎች ይጠቅማልና።" ይለናል፡፡ ኢንሻአላህ እንተዋወስ፡፡

አላህ ጀነትን ሲፈጥራት የሰው ልጆች በሚጠሉት ነገሮች የተከበበች አደረጋት፤ ጀሃነምን ደግሞ የሰው ልጆች ስሜት በሚወደው ነገር የታጠረች አደረጋት፡፡ ለዚህ ነው ታዲያ ብዙ ሰዎች ለኢባዳ ሰነፍ ለማእሲያ (ለወንጀል)ታታሪ የሚሆኑት፡፡ አላህ ከነዚህ አይነት ሰዎች ይጠብቀን፡፡ ውድ ወንድሞቸና እህቶቸ እስኪ ሁላችንም ራሳችንን እንጠይቅ፡፡ ማንኛውም አላህ የማይወዳቸው ነገሮች ለሰው ልጆች ጠቃሚ ናቸው? ፈጽሞ ጠቃሚ አይደሉም እንደምትሉ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ሱብሃነላህ የሰው ልጅ ግን የሚጠቅመውን ትቶ የማይጠቅመውን ለምን ይሰራል? አዎ ግልጽ ነው ኢብሊስ ለእነቱላህ አለይህ ስለሚያታልለውና ስለሚጫዎትበት ነው፡፡ ግን የአላህ ወልዮች (ወዳጆች)በፍፁም ለሸይጧን አይታለሉም፡፡ ምክንያቱም አሱ ግልፅ ጠላታቸው እንደሆነ ሙሉ እምነት አላቸውና፡፡ ሙዚቃን ምሳሌ ብናደርግ ዘጠና ዘጠኝ በመቶ የሚሆነው የሙዚቃ አይነት ለዚና (ለዝሙት)የሚጠራ የሸይጧን ከበሮ አንጂ ሶላት እንድንሰግድ፣ ዘካ አንድንሰጥ፣ የቲሞችን እንድንከባከብ፣ የወላጆችን ሃቅ አንድንጠብቅ፣ የሚናገር ሙሃደራ አይደለም፡፡ ሮማንቲክ ፊልም ብናይ ደግሞ አንዲት ሴት ባሏን አንዴት እንደምታታልለው እንደምትዋሸው፣ ዚና እንዴት ቀላል አንደሆነ ብቻ አጅግ ለሰው ልጆች ኑሮ ብጥብጥና ንትርክ ዋና መንስኤ የሚሆን ታላቅ የሸይጧን መሰብሰቢያ ደሴት ነው፡፡ ሱብሃነላህ ግን ከዚህ ላይ ልብ ልንል የሚገባን ነገር ሙስሊሞች ሆነን ነገ የውመልቂያማ የስራ መዝገባችን ሲሰጠን በሁሉም ስራችን ስንጠየቅ በሰጠን ጊዜም አንጠየቃለንና አላህ በማይዎደው ነገር ጊዜያችንን በማጥፋት የዚህንም ሆነ (የመጨረሻው አገር) የአሄራ ህይዎታችንን አናበላሽ!!
ከዚህ ጋር አያይዠ ሌላ ጥያቄ ራሳችን አንጠይቀና፤ ሙስሊሞች ነን ብለን ሁሌም እናዎራለን ግን ኢስላም ማለት ምን ማለት እንደሆነ ብንጠይቅ ትክክለኛ እውቀት ያለን ስንቶቻችን ነን? ሱብሃለነላህ ግን ሙስሊም ነኝ የምንልለለትን እምነት(ኢስላምን) አለማዎቅ እጅግ አሳፋሪ ነው፡፡ ጭንቅላታችን ውስጥ የሞላው ነገር ቢታይ ግን ከነብያችን (ሰ.አ.ወ) ሲራ (የህይዎት ታሪክ)ይልቅ ፈፅሞ የማይጠቅም ታሪክና ልቦለድ፣ ከሰሃቦች ስሞች ይልቅ የአርቲስቶችና የአክተሮች ስም፣ ከቁርዓን ይልቅ ሙዚቃ ብቻ ፈጽሞ ኢስላማዊ ያልሆነ ማንነታችንን ይዘን በተቀመጥንበት ተኝተናል፡፡ ግን ግን በአሁኑ ሰአት፣ ደቂቃና ሰከንድ መለከል መውት (የሞት መላይካ ወይም አዝራኤል) መጥቶ ዛሬ ሩህህን(ሽን) ላወጣ መጥቻለሁና ዝግጁ ነህ(ነሽ) ቢለን መልሳችን ምን ይሆን? አዎ ራሳችንን አናቃለን! ስለዚህ በቻልነው አቅም ልጅም ሆነ ሚስት (ባል)፣ አባትም ሆነ እናት፣ ገንዘብን ሆነ ስልጣን በማይጠቅምበት እለት በቻልነው አቅም ሁሉ ሙሉ ሃይላችንን አሟጠን ስንቃችንን ልናዘጋጅ የግድ ነው!!

ሙእሚኖች በኢስላም ሸሪአ ላይ ሁነው ሁለት ክንፍ አንዳለው በራሪዎች ይበራሉ፡፡ አንደኛው ክንፋቸው አላህ እንዳይቀጣቸው ጀሃነብን (እሳትን) በመፍራት ሌላኛው ደግሞ አላህ ጀነት እንዲያስገባቸው ተስፋ በማድረግ ይችን የሙስሊሞች እስርቤት የሆነችውን ዱንያ ያሳልፋሉ፡፡ አላህ ሁላችንንም ኻቲማችንን (መጨረሻችንን) ያሳምርልንና በዚህ ሁለት ክንፎቻቸው የዱንያን ጊዜያዊ ቆይታ አጠናቀው ወደማይቀረው አለመል አኼራ ይሄዳሉ፡፡ ሱብሃነላህ አላህ አደምነ (አለይሂ ሰላም)ከፈጠረው በኋላ ሃዋን መቀናጆ አድርጐ ጀነት ውስጥ ነበር አንዲኖሩ ያስቀመጣቸው፡፡ ኢብሊስ ለእነቱላህ አለይህ (የአላህ እርግማን በሱ ላይ ይሁንና)አሳስቷቸው ወደዝች ምድር ባይመጡ ኑሮ ሁላችንም ዛሬ ጀነት ውስጥ ነበርን፡፡ ከዚህ ላይ ታዲያ አንድ የምንማረው ነገር አለ፡፡ ይህም ምንድነው ሁላችም አገራችን ጀነት ነው፡፡ ስለዚህ ጀነት ልንገባ የምችለው ቁርዓንንና ቀጥተኛውን የረሱል (ሰ.አ.ወ)ሸሪዓ አጥብቀን ከያዝን ብቻ ነው፡፡ ካልሆነ ግን ወደማንፈልገው አገር ሳንወድ በግድ መወርወራችን አይቀሬ ነው፡፡ አላሁመ ነጂና ሚነ ናር፡፡ (አላህ ከሳት ይጠብቀን) አሚን፡፡

ይህ መልእክት ትክክል ከሆነ ከአላህ ነው፡፡ ስህተት ካለበት ግን ከእኔና ከሸይጧን ነው፡፡ አላህ ስራችንን ንፁህና ተወዳጅ ያድርግልን፡፡ አሚን
ሱብሃነከሏሁመ ወቢሃምዲከ ወተባረከ አሽሃዱ አንላኢላሃ ኢላ አንተ አስተኽፊሩከ ወአቱቡ ኢለይክ።

Tuesday, February 24, 2009

ጀዛከላህ ብራዘር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ ያ አህለል ሙዕሚኒን፡፡

ቃለሏሁ ተኣላ ፊልቁርዓኒል ከሪም "
وَٱلۡعَصۡرِ (١) إِنَّ ٱلۡإِنسَـٰنَ لَفِى خُسۡرٍ (٢) إِلَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّـٰلِحَـٰتِ وَتَوَاصَوۡاْ بِٱلۡحَقِّ وَتَوَاصَوۡاْ بِٱلصَّبۡرِ (٣)
"በጊዜያቱ እምላለሁ፤ ሰው ሁሉ በእርግጥ በከሳራ ወስጥ ነው፡፡ እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሰሩት፣ በእውነትም አደራ የተባባሉት፣ በመታገስም አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ፡፡"
ይለናል፡፡ ኢማሙ ሻፊኢይ ረሂመሁሏህ ስለዚች ሱራ ሲናገሩ "አለህ ይችን ብቻ ሱራ አውርዶ ሌላ ሱራዎችን ባያወርድ በቂ ነው፡፡ አላህ ነገ የውመልቂያማ ሱረቱል አስር የምትባል ሱራ አውርጀላችሁ ነበር ለምን አላመናችሁም ቢል እንኳን በቂ ነው፡፡" አሉ፡፡ ምክንያቱም አርካኑል ኢማንና አርካኑል ኢስላምን የያዘች ስለሆነች፡፡እንዲሁም አንድ ሰው ጀነት ለበግባት የሚስችሉትን መመዘኛዎች ስለያዘች፡፡

አላህ በምንሰራው ማንኛውም ስራ ኢህላስ እንዲኖረን በብዙ አንቀፆች አንዲሁም ተወዳጁ ነብያችን ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)በሃዲሳቸው አስተምረውናል፡፡ ዛሬ ይህን ፅሁፍ ለማዘጋጀት የፈለኩበት ምክንያትም አንድ ውድ ሙስሊም ወንዲሜ ስለዚህ ዌብ ሳይት ከሰጠኝ አስተያተት በመነሳት ነው፡፡ አላህ ኸይር ጀዛህን በጀነተል ፊርደውስ እንዲከፍልህ እየለመንኩ አለህ ሁላችንንም ዲነል ኢስላምን እንዲያሳውቀን፣ ቀጥተኛውን መንገድ እንዲመራን፣ ከአዛብ ቅጣት አድኖ ጀነትን ያለ ሂሳብ ግቡ ከሚባሉት ሰዎች እንዲያደርገን አለምነዋለሁ፡፡ ግን ለዚህ ታላቅ ስጦታ ምን አይነት ዝግጅት አድርገናል? ምን ያክል በቂ ስንቅ ሰንቀናል? ከልባችን እየተዘጋጅን ነው ወይስ እየቀለድን? አላህን በመፍራት እያነባን ወይስ በረባና ባልረባው እየሳቅን? እስኪ ራሳችንን እንጠይቅ? ምን ላይ ነው ያለነው? አዎ ጀነት በስራ ብቻ ሳይሆን በአላህ እዝነት ጭምር ነው የምትገኝ፡፡ ግን ግን አላህ የሚያዝንላቸው ሰዎች ልክ እንደኛ ቀላጆችን ወይስ ቀን በፃም ሌሊት በእንባ የአላህን ምህረት እየለመኑ ቁመው የሚያድሩ ሰዎች? ስራቸውን ለአላህ ብለው ለሚሰሩ ወይስ ለዩልኝ ብለው ለሰሩት? ጀነት ለነማን እንደሆነች አላህ እሱ ብቻ ያውቃል፡፡

አላህ ከነዚያ ከደጋግ ባሮቹ እንዲያደርገን እየለመንኩ እኔንም እናንተንም ላስታውስ የምፈልገው ግን እጅግ በዱንያ እንቅልፍ ውስጥ ተኝተናልና እስኪ እንንቃ! እንንቃ! ጊዘው አሁን ብቻ ነው፡፡ ዛሬ የስራ ጊዜ ነው፡፡ ሰከራተል መውት ሳይዘን በፊት እጅግ ጠንክረን ልንሰራ ይገባል፡፡ አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራን፡፡ አላህን በእውነት ከሚገዙት ሰዎች ያድርገንና፡፡ አሚን
ወሃዛ ወቢላሂ ተውቅ፤ ወሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ፡፡

የቁርዓንን ትርጉም መረዳት...

ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሂም፡፡በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ፡፡ሰላምና ደህንነት በእናንተ ላይ ይሁን፡፡

ውድ ወንድሞቸ፣ እህቶቸ፣ አባቶቸና እናቶቸ፡፡ አልሃምዱሊላህ ዛሬ ደግሞ የአላህ ፈቃድ ሆኖ እነዚህን የቁርዓን አንቀጾች ተርጉሜ ሳቀርብላችሁ፤ አላህ በሰማነው የምንጠቀምበት እንዲያደርገን እየለመንኩ ነው፡፡ አላህ ቁርዓንን በተወዳጁ ነብያችን ሰላሁ አለይሂ ወሰለም በኩል ለአለማት ደህንነትና እዝነት ከ1429 ዓመት በፊት አውርዶልናል፡፡ ይህ ቁርዓን ግን እጅግ ተወዳዳሪ የሌለው ለመሆኑ ራሱ ቁርዓን ከመመስከሩ በተጨማሪ ዛሬ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የዓለም ሳይንቲስቶች የፈጣሪ ቃል ለመሆኑ በርካታ ማስረጃዎችን አግኝተዋል፡፡ በእርግጥ ቁርዓን የሳይንስ መጽሃፍ አይደለም፡፡ ግን የቁርዓንን አምላካዊ ቃልነት ላልተረዱ ሰዎች ጥሩ ግንዛቤን ይሰጣል፡፡ የቁርዓንን ትርጉም በመረዳት ተፈኩር ማድረግ (ማስተንተን) ለኢስላም ጠንካራ እምነት እንዲኖረን እጅግ ይረዳናል፡፡ የዛሬ 1429 ዓመት የወረደው ይህ የአላህ ቃል ያልዳሰሰው የህይዎት ክፍል የለም፡፡ በአጠቃላይ ይህ ቁርዓን ለአለም ህዝቦች እዝነት ከጨለማ ወደ ብርሃን እንዲመራን የወረደ በመሆኑ አምነንበት ልንሰራበት የግድ ነው፡፡


እጅግ አዛኝ የሆነው አላህ ሁላችንንም በጀነተል ፊርደውስ እንዲሰበስበን እለምናለሁ፡፡
ወቢላሂ ተውፊቅ ወሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ፡፡


የቅዱስ ቁርዓን አማርኛ ትርጉም

ሱረቱ አል-በቀራህ (የላም ምዕራፍ) አማርኛ ትርጉም

አስደንጋጩ ፍፃሜ (Life after death)

The Understanding of ESA or JESUS the son of Marry In the Quran and Bible

Eslamawy Wendmamachnet (By Bedru Hussen) (Making any kind of copy is strictly forbidden)

EMAN Yelewt Mistir (by Bedru Hussen) (Making any kind of copy is strictly forbidden)

Le-emnetih Min Aberkitahal (by Yaseen Nuru) (Making any kind of copy is strictly forbidden)

ወዳጆችን እንገናኝ (በኡስታዝ ያሲን ኑሩ) (Making any kind of copy is strictly forbidden)

Ostaz Yasin Nuru (Please fear Allah don't download any of these Videos)

TEWHID (Islamic Monothesim)

Read and Listen Holly Quran

Quran Explorer - [Sura : 1, Verse : 1 - 7]

visiters map